መ.ኮ.ዲ.ድ የታማኝ ግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ተበረከተለት፤

መ.ኮ.ዲ.ድ የታማኝ ግብር ከፋይ፣ 2ኛ ደረጃ ዕውቅና የምስክር ወረቀት ከገቢዎች ሚኒስቴር ተበረከተለት፤

በ2016 በጀት አመት መከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ግብሩን በወቅቱና በአግባቡ በመክፈል ለታክስ ገቢ አሰባሰብ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ታማኝ ግብር ከፋይ በመባል የ2ኛ ደረጃ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ከገቢዎች ሚኒስቴር ተበረከተለት፡፡ በቦታው በመገኘት ሽልማቱን የተረከቡት የድርጅቱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ኮ/ል ኢ/ር ፅጋቡ ገ/ማሪያም ናቸው፡፡ ሽልማቱ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አገር ከመጠበቅ ጎን ለጎን በኮንስትራክሽን ዘርፉ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑን ድርጅቱ አስመስክሯል፡፡